ኢትዮጵያ – የአባይ ወንዝ ባለቤትነት ጉዳይ – Kidane_A
ኢትዮጵያ – የአባይ ወንዝ ባለቤትነት ጉዳይ ኪዳኔ ዓለማየሁ መግቢያ፤ በጥንቱ ዘመን የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። ባሁኑ ጊዜ ግን በተለይ ግብጽ የአባይን ወንዝ እንደ ግል ንብረቷ በመቁጠር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ለመጠቀም የምታከናውነውን ጥረት መቃወም ብቻ ሳይሆን ማስፈራራትም ይቃጣታል። እንደሚታወቀው በየድረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፣ ትችቶችና አስተያየቶች …